Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከ240 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በበልግ እርሻ እየለማ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ከ240 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በበልግ እርሻ እየለማ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር ማንደፍሮ አስላከ (ዶ/ር) ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደተናገሩት÷ በበልግ ከሚለማው መሬት ከ4 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል።

ስንዴን ጨምሮ ዋና ዋና ሰብሎች በበልግ እየለሙ መሆናቸውን ገልጸው÷ ከበልግ እርሻ ከታሰበው በላይ ምርት እንደሚገኝ የሚያሳይ ነው ብለዋል።

በዙፋን ካሳሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.