በ24 ተቋማት የተገነቡ የስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍሎች ተመረቁ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በ10 የፌዴራል ተቋማት፣ በ12 የክልል ርዕሳነ መስተዳድር እና በሁለቱ የከተማ አስተዳድር ከንቲባ ጽ/ቤቶች የገነባቸውን 24 የስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍሎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
ሚኒስቴሩ ሁሉንም ስማርት ክፍሎች በዛሬው ዕለት በተመሳሳይ ሰዓት በቨርቹዋል ዘዴ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ከንቲባዎች፣ ሚኒስትሮች፣ የተቋማት መሪዎች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ነው ያስመረቀው።
የተቋቋሙት የስማርት ክፍሎች የዲጂታል አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን ቁጥር ከፍ በማድረግ የተገልጋዩን ጊዜ፣ ገንዘብ እና ጉልበት ከመቆጠብ አኳያ ጉልህ ሚና ይኖራቸዋል።
በመሰል የተማከለ የዲጂታል መሠረተ ልማት የተቋማትን የመረጃ ልውውጥ ውጤታማነት ያሳድጋል።
ከዓለም ባንክ በተገኘ 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ የተገነቡት የስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍሎች ግንባታ የተጠናቀቀው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ነው።
በመራኦል ከድር