Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩትን ጎበኙ፡፡

ኢንስቲትዩቱ ከምድር እስከ ህዋ ድረስ የሚገኙ መረጃዎችን በመተንተን የምርምር ሥራዎችን የሚያከናውን ተቋም መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

የምርምር ሥራዎቹ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እየተተነተኑ ቅድመ ትንበያና የትንበያ ሥራዎችን በመሥራት ለሚመለከታቸው ተቋማት እንዲጠቀሙበት ያስችላል ተብሏል፡፡

የጂኦ ስፓሻል ጥናትና ምርምር በተለያዩ ዘርፎች የተዋቀረ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በዛሬው ጉብኝትም በየሥራ ክፍሎቹ የሚከናወኑ የመረጃ ትንተና እና ምርምር ሥራዎች ምልከታ ተደርጓል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.