Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 2ኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2ኛ ዙር ክልላዊ የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ማስጀመሪያ በወላይታ ዞን ጠበላ ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ ይገኛል።

እድሜያቸው ከአምስት አመት በታች ለሆኑ ህፃናት ከግንቦት 22 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ቤት ለቤት የተቀናጀ የፖሊዮ መከላከያ ክትባት ይሰጣል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ እና ፋይናንስ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ነብዩ ቤዛ እንዳሉት፤ ክትባቱ ለ1 ነጥብ 4 ሚሊየን ሕጻናት ይሰጣል።

በተቀናጀ የክትባት ዘመቻው የወባ በሽታ መከላከል እና ኤምፖክስ የተባለ በሽታም እንዳይስፋፋ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራም አመልክተዋል።

በቤት ለቤት ዘመቻ ወቅትም የእግር መቆልመም ችግር ያጋጠማቸውን ህጻናት በመለየት በአርባምንጭ ሆስፒታል ሕክምና እንዲያገኙ የሚሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በፌስቱላ ምክንያት የተጎዱ እናቶችም በኦቶና ሪፌራል ሆስፒታል  ሕክምና ያገኛሉ ብለዋል።

በኡሱማን መሐመድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.