የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሻርጃህ ከተማ በረራ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሻርጃህ ከተማ በረራ ጀምሯል።
ዛሬ ማምሻውን የበረራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአየር መንገዱ ተከናውኗል።
በመርሐ ግብሩ ላይ እንደተገለጸው፤ አየር መንገዱ ወደ ሻርጃህ ከተማ በሳምንት አራት ጊዜ በረራ ያደርጋል።
በመራኦል ከድር