የንግዱ ማኅበረሰብ ለሀገራዊ ብልጽግና የሚያደርገውን ተሳትፎ ማጠናከር አለበት – ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የንግዱ ማኅበረሰብ ለሀገራዊ ብልጽግና መረጋገጥ የሚያደርጉትን ተሳትፎ አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል አሉ፡፡
የፌደራል የንግዱ ማኅበረሰብ አካላት ሀገራዊ የምክክር መድረክ “ለሁለንተናዊ ብልጽግና የንግዱ ማኅበረሰብ ሚና” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ነው።
በዚሁ ወቅት ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር፤ በሁሉም ክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች በተካሄዱ መድረኮች ከ600 ሺህ በላይ የንግዱ በማኅበረሰብ አባላት መሳተፋቸውን አውስተዋል፡፡
የንግዱ ማኅበረሰብ ለሀገር ግንባታ፣ ለዜጎች ኑሮ መሻሻልና ለኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ የጎላ ነው ብለዋል፡፡
ይህን ለማጠናከርም መንግሥት ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር በይበልጥ ተቀራርቦ እንደሚሠራ ተናግረዋል።
የንግዱ ማኅበረሰብ አካላት በሀገራዊ ልማት የሚያደርጉትን ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉም አሳስበዋል።
ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ ጤናማ የገበያ ሥርዓት እንዲኖር እንዲሁም በዓለም አቀፍ ንግድ ተወዳዳሪ ለመሆን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
በኃይለማርያም ተገኝ