Fana: At a Speed of Life!

የከተሞች ልማታዊ የሴፍቲኔት ሥራ ፕሮጀክት ዐውደ ጥናት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት እና የሥራ ፕሮጀክት የልምድ ልውውጥና የዐውደ ጥናት መድረክ በኮምቦልቻ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

መድረኩ እየተካሄደ የሚገኘው፤ “ተጠቃሚዎቻችንን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በማሸጋገር የሀገራችንን ብልጽግና ዕውን እናደርጋለን” በሚል መሪ ሐሳብ ነው፡፡

የሴፍቲኔት መርሐ ግብር ከታለመለት ግብ አንጻር ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በመድኩ ላይ ባደረጉት ንግግር አንስተዋል፡፡

የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ መሐመድ አሚን በበኩላቸው፤ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የከተማ ነዋሪዎችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዜጎች ከተረጂነት አስተሳሰብ ተላቅቀው በዘላቂነት አምራች የሚሆኑበትን መንገድ መከተል እንደሚገባም በመድረኩ ተገልጿል፡፡

በቤዛዊት ከበደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.