Fana: At a Speed of Life!

በ951 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ በደገሃቡር ከተማ በ951 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባውን የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ የክልሉ መንግሥት የሕዝቡን መሠረታዊ ችግሮች ለመቅረፍ በትኩረት እየሠራ ነው።

የንፁህ መጠጥ ውኃ ሽፋንን በተመለከተም በከተሞች 51 በመቶ እንዲሁም በገጠር 48 በመቶ መድረሱን አብራርተዋል፡፡

በክልሉ የውኃ ተደራሽነት እየጨመረ በመምጣቱ የሕዝቡ ድርቅ የመቋቋም አቅም እየጎለበተ ነው ብለዋል፡፡

ዛሬ የተመረቀው ፕሮጀክትም ለ20 ዓመታት አገልግሎት መስጠት እንደሚችል ጠቅሰዋል፡፡

ከ100 ሺህ በላይ ወገኖችን ተጠቃሚ የሚያደርገው ይህ ፕሮጀክት፤ የከተማዋን ነዋሪዎች የዘመናት የንፁህ መጠጥ ውኃ ጥያቄ መመለሱ ተመላክቷል፡፡

በተስፋዬ ኃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.