Fana: At a Speed of Life!

የዲጂታል ሚዲያውን በማጠናከር መረጃዎች ለማህበረሰቡ በፍጥነት ማድረስ ይገባል – አቶ ሞገስ ባልቻ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ የዲጂታል ሚዲያውን በማጠናከር ተአማኒነት ያላቸውን መረጃዎች ለማህበረሰቡ በፍጥነት ማድረስ ይገባል አሉ።

የተደራጀ ኮሙኒኬሽንና ሚዲያ የሀገራዊ መግባባት ካስማ፣ የትውልድ ግንባታ መሰረት በሚል መሪ ሀሳብ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

አቶ ሞገስ ባልቻ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር፤ የሚዲያ ባለሙያዎች እውነትን ይዘው አንድነትን የሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ በሀላፊነት መስራት አለባቸው ብለዋል።

በተገኙ ስኬቶች ሳንዘናጋ የሚያጋጥሙንን ተግዳሮቶች በማለፍ የመገንዳችን መጨረሻ ላይ ለመድረስ በጋራ ተባብረን መስራት ይጠበቅብናል ሲሉም ተናግረዋል።

ተልዕኮን ከመፈፀም ረገድ እንዲሁም በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ሁሉም የበኩሉን መውጣት እንዳለበት ገልጸዋል።

ከህዝብ ጋር በሚደረጉ የውይይት መድረኮች ገንቢ ሀሳብ አግኝተናል ነው ያሉት።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ እናታለም መለስ በበኩላቸው ጊዜው የዲጂታል በመሆኑ ሚዲያዎች እውነታውን ተከትለው መዘገብ እና ለማህበረሰቡ መረጃዎችን በፍጥነት ማድረስ አለባቸው ብለዋል።

ዓላማን በመገንዘብ በሚዲያው ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ይገባል ሲሉም አመላክተዋል።

በወንድማገኝ ጸጋዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.