Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ወሎ ዞን የተለያዩ ከተሞች የዒድ አል አድሃ በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን የተለያዩ ከተሞች የ1 ሺህ 446ኛው ዓመተ ሂጅራ የዒድ አል አድሃ በዓል እየተከበረ ነው፡፡

በደሴ ከተማ የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሆጤ ስታዲየም በጋራ የሶላት ሥነ-ሥርዓት አከናውነዋል፡፡

እንዲሁም በኮምቦልቻ ከተማ የዒድ አል አድሃ በዓል በተለያዩ ሐይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች እየተከበረ ነው።

በከተማዋ የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ከማለዳው ጀምሮ የዒድ ሶላት በሚከናወንባቸው ሥፍራዎች በመሰባሰብ ተክቢራ አድርገዋል፡፡

በተመሳሳይ በወረባቦ ወረዳ የዒድ አል አድሃ በዓል በድምቀት በመከበር ላይ ሲሆን፤ ሕዝበ ሙስሊሙም በጠዋት ወደ ሰገዳ ቦታ በማምራት የሶላት ሥነ-ሥርዓቱን አከናውኖ ወደ ቤቱ ተመልሷል።

በከድር መሐመድ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.