1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሐረሪ ክልል እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሐረሪ ክልል በተለያዩ ሀይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በክልሉ በገጠርና ከተማ ወረዳዎች የሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች ከማለዳው ጀምሮ ሐረር ከተማ ወደሚገኘው አሚር ሀቡባ ስታድየም በመሰባሰብ በዓሉን በኢድ ተክቢራ እና በሶላት እያከበሩት ነው።
በበዓሉ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ የእምነቱ ተከታዮች እንዲሁም የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
በተስፋዬ ኃይሉ