Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል የዒድ አል አድሃ በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 1 ሺህ 446ኛው ዓመተ ሂጅራ የዒድ አል አድሃ በዓል በሶማሌ ክልል የእስልምና እምነት ትዕዛዛትን በማከናወን እየተከበረ ነው፡፡

የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች፣ የእልምና እምነት አባቶች እና መምህራን እንዲሁም የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በጂግጂጋ ከተማ የሶላት ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል፡፡

የዒድ አል አድሃ የዕርድ በዓል እንደመሆኑ በጋራ ከሚሰገደው ሶላት በኋላ ዕርድ ይከናወናል፡፡

ለበዓሉ ከሚሠናዳው አጠቃላይ ዝግጅትም አንድ ሦስተኛው ለተቸገሩ ወገኖች እንደሚውል የእምነቱ መምህራን ይገልጻሉ፡፡

ዒድ አል አድሃ የመተዛዘን እና የመረዳዳት በዓል እንደሆነ ይታወቃል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.