ዒድ አል አድሃን በመደጋገፍ ማክበር ይገባል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 1 ሺህ 446ኛው ዓመተ ሂጅራ ዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በጋምቤላ ከተማና አካባቢዋ በሕዝበ ሙስሊሙ ዘንድ እየተከበረ ነው።
የጋምቤላ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሁሴን ካዩራ እንዳሉት፤ በዓሉን ስናከብር አቅመ ደካሞችን በማሰብና በመደገፍ ሊሆን ይገባል፡፡
ዕለቱ ሁሉም የእምነቱ ተከታዮች እንደየአቅማቸው እርድ በመፈፀም ያለው ለሌለው በማካፈል እኩል ተደስቶ እንዲውል የሚደረግበት ታላቅ በዓል እንደሆነም አመልክተዋል።
እኛም በዓሉን ስናከብር የእምነቱ አስተምህሮ በሚያዘው መሰረት አቅመ ደካሞችን በማሰብና ያለው ለሌለው በማካፈል በጋራ ልናከብር ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በበዓሉ ወቅትም የእርስ በርስ ትስስርና አንድነትን የሚያጠናክሩ እሴቶቻችንን አጉልተን በማሳየት በደስታ ልናሳልፍ ይገባል ነው ያሉት፡