Fana: At a Speed of Life!

የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በጎንደር እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በጎንደር ከተማ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ ሶላት እና ተክቢራን ጨምሮ በተለያዩ ኃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ሲከበር የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከበር በችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖች በመርዳትና በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ ተመላክቷል።

በከተማዋ በሚከናወኑ የሰላምና የልማት ስራዎች የነቃ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው ህዝበ ሙስሊሙ፤ በቀጣይም ለዘላቂ ሰላም እንዲሰራ ተጠይቋል።

በምናለ አየነው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.