አርሰናል የጋብሬል ማግሀሌስን ውል አራዘመ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አርሰናል የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹን ጋብሬል ማግሀሌስን ውል እስከ ፈረንጆቹ 2029 ማራዘሙን ይፋ አድርጓል፡፡
ብራዚላዊው የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ጋብሬል ማግሀሌስ ከአምስት ዓመት በፊት ከሊል ወደ አርሰናል መቀላቀሉ ይታወሳል፡፡
ማግሀሌስ መድፈኞቹን ከተቀላቀለበት ጊዜ ጀምሮ ለአርሰናል 210 ጫወታዎችን አድርጎ 20 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል፡፡