Fana: At a Speed of Life!

ተተኪ አመራር ለማፍራት ወጣቶች ላይ እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተተኪ አመራር ለማፍራት ወጣቶችላይ እየተሠራ ያለውን ሥራ አብራርተዋል፡፡

በማብራሪያቸውም እስከ አሁን እያመጣናቸው ያሉ ውጤቶች በበቂ ሁኔታ ተኪ አመራሮች ማፍራት ካልቻልን፤ የአመራር መዛነፍ አለ፤ የጉዞ መደነቃቀፍ አለ፤ ውጤቱም ከግብ አይደርስም ብለዋል፡፡

የአንድ አመራር መለኪያው በበቂ ሁኔታ ተኪዎች የማዘጋጀትና የመፍጠር አቅሙም ጭምር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ወጣቶችን ማዘጋጀት አስፈላጊ እንደሆነ በተግባር እናውቀዋለን ሲሉ ተናግረዋል።

ይህን ስለምንረዳም የወይፈኑን ጉልበትና የበሬውን ብልሃት ደምረን ነው ያለውን መከራ የምናርሰው ሲሉ አብራርተዋል፡፡

ነገን በማሰብ በመንግሥትም ሆነ በፓርቲ ወጣቶችን መሠረት በማድረግ በሥራ እና በሥልጠና ትኩረት መሰጠቱን አንስተዋል፡፡

በሚመሩት ካቢኔ ውስጥ የወጣቶች ተሳትፎ መኖሩን ጠቅሰው፤ በታቀደ መንገድ ሀገር አሻጋሪ ወጣቶች ላይ እየሠራን ነው ብለዋል በማብራሪያቸው፡፡

መሪነት የዕውቀት ብቻ ሳይሆን የክኅሎትና የጥበብ ጭምር መሆኑን አስገንዝበው፤ ለዚህም መውረድና መውጣት ያስፈልጋል፤ በዚህ መንገድ ማለፍ ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

ኢትዮጵያ ወደፊት የመሪ ጉዳይ ያሳስባታል ብዬ አልሰጋም ሲሉም ተናግረዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.