በመዲናዋ ከ2 ሺህ በላይ የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ምረቃ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ስድስተኛ ዙር የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ምረቃ ሥነ ሥርዓት እያካሄደ ነው፡፡
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አበቤን ጨምሮ ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
ተመራቂ ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ሲያሰለጥናቸው የቆዩ ናቸው፡፡
ተመራቂዎቹ በንድፈ ሃሳብ፣ በወታደራዊ ሳይንስና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ለሁለት ወራት ስልጠናቸውን በመከታተል በብቃት ያጠናቀቁ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
አጠቃላይ ተመራቂዎቹ 2 ሺህ 74 ሲሆኑ ÷ ከዚህ በፊት የመጀመሪያ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ የትምህርት ደረጃ ያላቸው መሆኑ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ወቅት ተጠቅሷል፡፡
በመሳፍንት ብርሌ