Fana: At a Speed of Life!

የሀምበሪቾ ተራሮች የኢትዮጵያን የተፈጥሮና የባሕል ቅርስ የሚያሳዩ ተምሳሌቶች ናቸው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀምበሪቾ ተራሮች የኢትዮጵያን የተፈጥሮ እና የባሕል ቅርስ የሚያሳዩ ተምሳሌቶች ናቸው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሚገኙት አስደናቂ የተራራ ሰንሰለቶች  የብዝኃ ሕይወት ሃብት እና የታሪክ ዋጋን የተሸከሙ ናቸው ብለዋል።

ሀምበሪቾ ተራራ እና ከባቢው ከ16ኛው እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን በተከታታይ የከምባታ ነገስታት መቀመጫ በመሆን ማገልገሉን አስታውሰዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ዜጎች እና ከዓለም ዙሪያ የሚመጡ ጎብኚዎች አስደማሚውን የሀምበሪቾ ውበት እንዲመለከቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዚህም ጎብኚዎች በአካባቢው ሕዝብ እውቀትና ጉልበት የተሰራውን እና እርሳቸውም የወጡትን አስደናቂ 777 ደረጃ በመውጣት ራሳቸውን እንዲፈትኑ ጋብዘዋል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.