Fana: At a Speed of Life!

የሐረርን ታሪካዊ ከተማነት የሚመጥኑ በርካታ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ነው – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ3ኛው ምዕራፍ የጁገል ኮሪደር የለሙ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በዛሬው ዕለት ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል፡፡

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በዚህ ወቅት እንደገለጹት ÷ ከዚህ ቀደም ለጥንታዊቷ ሐረር ታሪኳን የሚመጥን ሥራ ባለመሰራቱ ለነዋሪው ብሎም ለጎብኚዎች ምቹ ሳትሆን ቆይታለች።

በተለይም የዓለም አቀፍ ቅርስ የሆነውን የጁገል ቅርስ ከተጋረጠበት አደጋ ለመታደግ ያለተጨማሪ በጀት በሕብረተሰቡና በተለያዩ ተቋማት ርብርብ ምሳሌ ሊሆን የሚችል ሥራ ተከናውኗል ብለዋል።

ቀደም ሲል በሁለት ምዕራፎች በተሰሩ ከ7 ኪሎ ሜትር በላይ የጁገል ኮሪደር መልሶ ልማት ቅርሱን ለጎብኚዎችና ለነዋሪዎች ምቹ በማድረግ ረገድ አበረታች ውጤት መመዝገቡን አንስተዋል።

በ3ኛው ምዕራፍ ከ6 ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍኑ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በፍጥነትና በጥራት መገንባታቸውን ጠቁመው÷ በመርሐ ግብሩ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል።

በጅጎል መልሶ ልማት የተገኙ ውጤታማ ሥራዎችን በሌሎች ዘርፎች በማስቀጠል የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ በትኩረት እንደሚሰራም አመልክተዋል።

በተስፋዬ ኃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.