Fana: At a Speed of Life!

ከኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ጋር በመዲናዋ ሁለንተናዊ ለውጦች ዙሪያ በትብብር ለመስራት ተስማምተናል  –  ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከኪነጥበብ ባለሞያዎች ጋር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለንተናዊ ለውጦች ዙሪያ በትብብር ለመስራት ተስማምተናል አሉ የአስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡

በአዲስ አበባ “ሀገር እና ጥበብ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ ከተማ አቀፍ የኪነጥበብ ባለሞያዎች  የማጠቃላይ መድረክ ተካሂዷል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ ኪነ ጥበብ ለሀገር እና ትውልድ ግንባታ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡

መድረኩ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች በአዲስ አበባ በሚከናወኑ የለውጥ ሥራዎች የሚኖራቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ከኪነጥበብ ባለሞያዎች ጋር በቀጣይ በመዲናዋ ሁለንተናዊ ለውጦች ዙሪያ በትብብርና በቅንጅት ለመራስት መግባባት ላይ መደረሱንም የከንቲባ ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሃላፊ ሚኤሳ ኤሌማ (ዶ/ር) ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.