ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ዛሬ ከመላው ኢትዮጵያ ከተወጣጡ የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፤ በዞን፣ በክልል እና ከተሞች ደረጃ ከተካሄዱ ውይይቶች የቀጠለ ውይይት በፌዴራል ደረጃ አካሂደናል ብለዋል።
መድረኩ በየደረጃው የተሰበሰቡ የንግዱ ዘርፍ ጉዳዮች እና ሐሳቦች በሀገር አቀፍ እቅዶች እና የልማት ግቦች ዝግጅት ግብዓት ይሆኑ ዘንድ ለማካተት የተዘጋጀ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡