የአትሌቶች ሁለንተናዊ ጥበቃ ፖሊሲ በኢትዮጵያ እንዲተገበር እየተሠራ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአትሌቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል”የአትሌቶች ሁለንተናዊ ጥበቃ ፖሊሲ” በኢትዮጵያ እንዲተገበር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን እየሠራሁ ነው አለ፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቲክ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር ስለሺ ስኅን በሰጡት መግለጫ፤ አትሌት ገለቴ ቡርቃ በመገናኛ ብዙኃን የገጠማትን ችግር መናገሯን ጠቅሰው፤ ለሀገራቸው ዋጋ የከፈሉ እና አሁን ችግር ውስጥ ያሉ አትሌቶች ቁጥር በርካታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ የአትሌቶችን ጥበቃ የሚደነግጉ ሕጎች ከ2023 ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆኑ ውሳኔ ማሳለፉንም አስታውሰዋል፡፡
በመሆኑም “የአትሌቶች ሁለንተናዊ ጥበቃ ፖሊሲ” በኢትዮጵያ እንዲተገበር እየሠሩ መሆናቸውን ነው ያስታወቁት፡፡
ችግሮች ከሴቶቹ ባሻገር በወንድ አትሌቶች ላይም በስፋት እንደሚስተዋሉ ጠቁመዋል፡፡
በአትሌት ገለቴ ቡርቃ ላይ የደረሰውን ጥቃት ያወገዘው ፌደሬሽኑ፤ ፍትሕ እንዲሰጣት ጠይቋል፡፡
አትሌቷ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ የገጠማትን ችግር በፍርድ ቤት ለመፍታት ጥረት እያደረገች እንደምትገኝ አውቃለሁ ያለችው የፌደሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት መሠረት ደፋር፤ ሕግ ለዚች የሀገር ባለውለታ ትክክለኛውን ፍትሕ እንዲሰጣት እጠይቃለሁ ብላለች፡፡
በወርቅነህ ጋሻሁን