Fana: At a Speed of Life!

ላፍቶ ሁለገብ የገበያ ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ8 ነጥብ 8 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈው ላፍቶ ቁጥር 2 ሁለገብ የገበያ ማዕከል ተመርቋል።

ማዕከሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ጋር በመሆን መርቀው ከፍተዋል።

ዘመናዊ የግብይት ሥርዓትን በማሣለጥ በጎ ሚና ይኖረዋል የተባለው የገበያ ማዕከሉ፤ የማቀዝቀዣ ክፍሎችን ጨምሮ ሱፐር ማርኬቶችና ዘመናዊ ሱቆችን አካትቷል።

ይህም ከዚህ ቀደም በከተማ አስተዳደሩ ከተገነቡት መሠል የገበያ ማዕከላት ልዩ እንደሚያደርገው ተገልጿል።

ማዕከሉ አምራች እና ሸማችን በቀጥታ በማገናኘት የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነትን እንደሚያስቀር ተነግሯል።

በሰለሞን ይታየው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.