Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ ወደ ሃይድራባድ የመጀመሪያውን የመንገደኞች በረራ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ሕንዷ ሃይድራባድ የመጀመሪያውን የመንገደኞች በረራ አስጀምሯል።
አየር መንገዱ ከአዲስ አበባ ወደ ሃይድራባድ በሳምንት ሶስት ጊዜ የሚያደርገውን የመንገደኞች በረራ በትናንትናው ዕለት ነው በይፋ ያስጀመረው፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች አውሮፕላን ሃይድራባድ ሲደርስም በከተማዋ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
አዲሱ በረራ በእድገት ላይ ያለችውን ሃይድራባድ ከተማ ከአዲስ አበባ እና ከሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ጋር የማስተሳሰር ሚናው ጉልህ እንደሚሆን ተመላክቷል።
ሃይድራባድ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ 6ኛ የሕንድ መዳረሻ ስትሆን ፥ በአሁኑ ወቅት በሳምንት ከ50 በላይ የመንገደኞችና የካርጎ በረራዎች ወደ ሕንድ እንደሚደረጉ ተመላክቷል።
ዴልሂ፣ ሞምባይ፣ ቤንጋሉሩ፣ አህምዳባድ እና ቺናይ ሌሎች የሕንድ መዳረሻዎች ሲሆኑ፥ የሀይድራባድ በረራ መጀመርም እያደገ ለመጣው የመንገደኞች በረራ ፍላጎት አማራጭ እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡
በታሪኩ ለገሰ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.