Fana: At a Speed of Life!

የአእምሯዊ ንብረት ምዝገባ ሥርዓትን ለማጠናከር እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃና ምዝገባ ሥርዓትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን፡፡

የባለስልጣኑ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኤሊያስ መሃመድ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ÷ የአእምሯዊ ንብረት ምዝገባ የፈጠራ ሥራዎችን ለማበረታታት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡

ለዚህም የአእምሯዊ ንብረት ምዝገባ እና ጥበቃ ቁጥርን ለማሳደግ እና ተደራሽነቱን ለማስፋት በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ባለፉት 11 ወራት ከ7 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የፈጠራ ሥራዎች የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃና ምዝገባ መከናወኑን አንስተዋል፡፡

የምዝገባ ሥራውም በፓተንት፣ በንግድ ምልክት፣ በቅጂና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ ላይ ያተኮረ መሆኑን ነው ያስረዱት፡፡

በኢትዮጵያ የፈጠራ ሥራዎችን በማስመዝገብ ረገድ የግንዛቤ እጥረት መኖሩን ጠቁመው ÷ ችግሩን ለመቅረፍ በትብብር እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የሕግ ማሻሻያ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ የገለጹት አቶ ኤሊያስ ÷ በዘርፉ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን የመፈረም ሥራ መከናወኑን አንስተዋል፡፡

የፈጠራ ሥራዎች ተገቢው ጥበቃ ተደርጎላቸው ለሀገር እድገት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ሕብረተሰቡ የበኩሉን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.