ለተሟላ ነፃነትና ኢኮኖሚያዊ እድገት የስራ ባህልን ማሳደግ ቁልፍ ጉዳይ ነው – ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለተሟላ ነፃነትና ኢኮኖሚያዊ እድገት የስራ ባህልን ማሳደግ ቁልፍ ጉዳይ ነው አሉ የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር “የስራ ባህልና ምርታማነት ለሀገር ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ሃሳብ ያዘጋጀው የፓናል ውይይት በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል።
ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ከዓለም ነባራዊ ሁኔታ ጋር አብሮ ለመራመድ ከስራ ባህል አስተሳሰብ ጀምሮ እስከ ተግባር መለወጥ ያስፈልጋል።
ለተሟላ ነፃነትና ኢኮኖሚያዊ እድገት የስራ ባህልን ማሳደግ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን አንስተው÷ የስራ ባህልን ለማምጣት የአስተሳሰብ እና የእይታ ለውጥ ማድረግ እንዲሁም በየአካባቢው ያለ ፀጋን መመልከት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ስራ መገለጫቸው የሆኑና ኢኮኖሚያዊ ህልውናቸውን ያረጋገጡ ዜጎች አንዲኖሯት የስራ ባህልን እያሳደገች እንደምትገኝ ጠቅሰው÷ ቀጣዩ ትውልድም በዚህ የታነፀ እንዲሆን በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰይፈ ደርቤ በበኩላቸው÷ ተቋማቸው የስራ ባህል ሊያሳድጉ የሚችሉ በርካታ ተሞክሮዎችን በማስተላለፍ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።
የፓናል ውይይቱም የስራ ባህል ለውጥ ማምጣት ላይ ከባለድርሻ አካላት ለመምከርና የጋራ አቋም ይዘው ለመስራትና ለማገዝ ያለመ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
በመድረኩ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ ከፌደራልና ከክልል ተቋማት የተውጣጣና ሌሎች ተጋባዥ ተሳታፊዎች እየተወያዩበት ይገኛል፡፡
በማርታ ጌታቸው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!