Fana: At a Speed of Life!

የአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ ስኬት ኢትዮጵያውያን በመደመር ያቀዱትን መተግበር እንደሚችሉ ያሳዩበት ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ ስኬት ኢትዮጵያውያን በመደመር ያቀዱትን መተግበር እንደሚችሉ ያሳዩበት ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ ÷ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር 805 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ችግኞች መተከላቸውን አብስረዋል፡፡

በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ታላቅ ተግባር ለፈጸመው የኢትዮጵያ ሕዝብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ይህ ድል በብዙ ሀገራት ሊታሰብ ይችላል፤ በቀላሉ ግን ሊከወን አይችልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ አርአያ መሆን እንደምትችል አስረድተዋል፡፡

የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ ስኬት ኢትዮጵያውያን በመደመር ያቀዱትን መተግበር እንደሚችሉ ያሳዩበት ሀገራዊ ንቅናቄ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በመርሐ ግብሩ ያሳየነውን አብሮነት በሌሎች ጉዳዮች በአንድነት በመቆም፣ በመደመርና ለልጆቻችን ተስፋን በመስጠት እናሳካው ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ክረምቱ ከገባ ጀምሮ እስካሁን 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞች መተከላቸውንም ተናግረዋል፡፡

በእመቤት ሲሳይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.