Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአዲስና ለማስፋፊያ አምራች ኢንዱስትሪዎች የመስሪያ ቦታ ቁልፍ አስረከቡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአዲስ እና ለማስፋፊያ አምራች ኢንዱስትሪዎች የመስሪያ ቦታ ቁልፍ አስረክበዋል።

ከንቲባዋ የንግዱን ማህበረሰብ እና አምራች ኢንዱስትሪዎችን ባወያየንበት ወቅት በቀረቡልን ጥያቄዎች መሰረት መልስ እየሰጠን እንገኛለን ብለዋል።

አዲስ አባባ ቀን ብቻ ሳይሆን ሌሊትም የሚሰራባት ከተማ እየሆነች መጥታለችም ነው ያሉት ከንቲባዋ።

በዛሬው ዕለትም ለአዲስና ለማስፋፊያ አምራች ኢንዱስትሪዎች ለሚቀርቡ የመስሪያ ቦታ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በተገባው ቃል መሰረት ግልፅ መስፈርት በማውጣት በመስፈርቱ ቅድሚያ ለሚገባቸው አምራች ኢንዱስትሪዎች የቁልፍ ርክክብ መደረጉን የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለፋና ዲጂታል ገልጿል።

የመስሪያ ቦታ ቁልፍ የተረከቡ አምራቾች አርዓያ የሚሆን ስራ በመስራትና ምርታማነትን በመጨመር እንዲሁም የስራ እድል በመፍጠር ገበያን ማረጋጋት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

ያለንን መሬትና የሰው ኃይል ተጠቅመን በእልህ ስኬታማ እንሁን ያሉት ከንቲባዋ÷ አምራቾችም ትልቅ ህልም በመያዝ ውጤታማ ሥራ ይጠበቅባቸዋልም ነው ያሉት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.