በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 2ኛው ዙር የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአርባ ምንጭ ከተማ ተካሂዷል።
መርሐ ግብሩን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እና የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሌሊሴ ነሜ (ኢ/ር) አስጀምረዋል፡፡
ንቅናቄው በዓለም ለ52ኛ፤ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ32ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን የአካባቢ ቀን መነሻ በማድረግ ”ጽዱ ኢትዮጵያን ባህል እናድርግ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የሚካሄደው፡፡
ሌሊሴ ነሜ (ኢ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት ፥ ለ6 ተከታታይ ወራት በሚካሄደው የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የሕግ ተተግባሪነትን ማረጋገጥ፣ የበጎ ፈቃድ ተግባራትና የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ይከናወናል፡፡
በማስተዋል አሰፋ