በመዲናዋ 350 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2018 በጀት ዓመት 350 ቢሊየን ብር ገደማ ተሰብስቧል አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡
ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የገቢ መሰረትን በማስፋትና የሚሰበሰብ ገቢ ፍትሃዊነትን በጠበቀ መልኩ እንዲሰበሰብ ለማድረግ በትኩረት ተሰርቷል፡፡
በዚህም በአዲስ አበባ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከተለያዩ የገቢ ምንጮች 350 ቢሊየን ብር ገደማ መሰብሰቡን ነው የገለጹት፡፡
የ2018 ገቢ አሰባሰብ ከ2017 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ116 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወይም የ50 በመቶ እድገት ማሳየቱን አመልክተዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለመዲናዋ ግብር ከፋዮች ምስጋና አቅርበዋል፡፡