ወራቤ ዩኒቨርሲቲ 1 ሺህ 561 ተማሪዎችን አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ፣ ሳምንታዊ እና የማታ መርሐ ግብሮች በድህረ ምረቃ ፕሮግራም ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 561 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
በመርሐ ግብሩ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ቶፊቅ ጀማል (ዶ/ር) አሁን ላይ የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል ብለዋል።
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በምርምር የታገዙ ውጤታማ ተግባራትን በስራ ለመግለጽ እየተጋ መሆኑን ጠቅሰው÷ የስልጠና ተቋማት የሀገር ብልጽግና እና እድገት ሊያረጋግጡ የሚችሉ ስራዎች ላይ አተኩረው መስራት ይኖርባቸዋልም ነው ያሉት።
በዚህም ዩኒቨርሲቲው ከ300 በላይ ለፖሊሲ አውጪዎች ግብዓት የሚሆኑ የምርምር ጽሑፎች ማሳተሙን አንስተዋል።
ምረቃ ሥነሥርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት÷ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የትምህርት ዘርፉን ለማሻሻል ብዙ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የትምህርት ጥራት ለማሻሻል ከታች ጀምሮ በጥራት ላይ ሲሰራ መቆየቱን አንስተው÷ እንደ ሀገር የተሰጠውን የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ የትምህርት ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቷልም ነው ያሉት።
ዩኒቨርሲቲው ከተመሰረተ ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ዓመታት ከ7 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን÷ ዛሬ በተካሄደው የስድስተኛው ዙር መርሐ ግብር ተመራቂዎች ከ90 በመቶ በላይ የመውጫ ፈተናውን ያለፉ መሆናቸው ተመላክቷል።
በይስማው አደራው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!