ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከጤና ባለሙያዎች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጤና ባለሙያዎች ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መረጃ፥ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የምናደርገውን ውይይት በመቀጠል ዛሬ ከጤና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አድርገናል ብለዋል።
በውይይቱም እድሎችን እና በጎ ርምጃዎችን ብሎም ክፍተቶችን እና ተግዳሮቶችን ዳሰናል ነው ያሉት።