በቱሪዝም ዘርፍ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመረጃ ስርዓት ማስፋት ይገባል – ሰላማዊት ካሳ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ በዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማሳደግ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመረጃ ስርዓት ማስፋት ይገባል አሉ።
በኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን የተዘጋጀውና ትኩረቱን ቱሪዝምና ቴክኖሎጂ ላይ ያደረገ ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
ሚኒስትሯ በመርሐ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት÷ ዋና ዋና የኢኮኖሚ ምንጭ ተብለው ከተለዩ ዘርፎች መካከል ቱሪዝም አንዱ መሆኑን አንስተዋል።
ኢትዮጵያ በርካታ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ሀብቶችና ባህላዊ እሴቶች ቢኖሯትም ከዘርፉ የሚገኘው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እምብዛም ሆኖ ቆይቷል።
ይሁን እንጂ የለውጡ መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት አዳዲስ መዳረሻዎችን የማልማት፣ ነባሮችን የማደስና ዘርፉን የማዘመን ስራዎች ተከናውነዋል።
በዚህም ትርጉም ያለው ለውጥ በማምጣት አበረታች ውጤት እንዲመዘገብ አስቻይ ሁኔታ ተፈጥሯል ያሉት ሚኒስትሯ÷ ዘርፉ ከሚያስገኘው ጠቀሜታና ካለው እምቅ ሀብት አኳያ አሁንም ብዙ ስራዎች ያስፈልጋል ብለዋል።
በተለይም በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመረጃ ስርዓት በማስፋት በቱሪዝም ዘርፍ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም መጨመር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ነጋ ወዳጆ በበኩላቸው÷ በክልሉ ያሉ የቱሪዝም ሀብቶችን የማስተዋወቅ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸው፤ ዛሬ የተጀመረው ፎረሙም የዚሁ አካል መሆኑን አስረድተዋል።
ፎረሙ በዋናነት በዘርፉ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ቴክኖሎጂዎች የሚተዋወቁበት፣ ተሞክሮ የሚቀሰምበትና ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያግዙ ውይይቶች የሚካሄዱበት እንደሆነ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!