ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከፕሬዚዳንት ትራምፕ የአፍሪካ ከፍተኛ አማካሪ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአፍሪካ ከፍተኛ አማካሪ ማሳድ ቦሎስ ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ የተካሔደው በአንጎላ ርዕሰ መዲና እየተካሄደ ካለው የአፍሪካ አሜሪካ የቢዝነስ ጉባኤ ጎን ለጎን ነው።
በውይይታቸውም ለበርካታ ዓመታት የዘለቀውን የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ መከረዋል፡፡
በተጨማሪም በቀጣናዊ የልማትና የሠላም ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ እና አሜሪካ ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሙሌ ታረቀኝ ገልጸዋል።
በተለይም በኢንቨስትመንትና የንግድ ዲፕሎማሲ ማዕቀፍ ሁለቱ ሀገራት በዘርፉ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማሳደግና ለማስፋት ከመግባባት ላይ መድረሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡