Fana: At a Speed of Life!

መቐለ 70 እንደርታ ከፕሪሚየር ሊጉ ወረደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ36ኛ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ መቐለ 70 እንደርታን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሊጉ እንዲቆይ ያስቻለችዉን ብቸኛ ግብ እዮብ ገብረማሪያም በመጀመሪያው አጋማሽ ከመረብ አሳርፏል።

ለ2018 ዓ.ም የውድድር ዘመን ለመቆየት የአቻ ውጤት በቂው የነበረዉ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተጋጣሚውን በማሸነፍ የውድድር ዓመቱን በድል አጠናቅቋል።

በሊጉ መቆየቱን ያረጋገጠው ኢትዮ ኤሌክትሪክ 44 ነጥብ በመሰብሰብ 12ኛ ደረጃን ይዞ የውድድር ዓመቱን ጨርሷል።

በሊጉ ለመቆየት የማሸነፍ አማራጭን ብቻ ይዞ ወደ ሜዳ የገባው መቐለ 70 እንደርታ የመጨረሻ ሳምንት የሊጉን ጨዋታ ተሸንፎ ወደ ከፍተኛ ሊጉ ወርዷል።

መቐለ 70 እንደርታ በውድድር ዓመቱ ካደረጋቸው 34 ጨዋታዎች 41 ነጥቦችን ሰብስቦ 15ኛ ደረጃ በመያዝ ከሊጉ ተሰናብቷል።

 

የ2017 ዓ.ም የውድድር ዓመት የኢትዮዽያ ፕሪሚየር ሊግ የመዝጊያ ጨዋታ ነገ ሲደረግ ሻምፒዮኑ ኢትዮዽያ መድን አስቀድሞ መውረዱን ካረጋገጠው ስሑል ሽረ ጋር ይገናኛል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.