Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል የኤሌክትሪክ ሃይል ተደራሽነትን ለማጠናከር እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጋምቤላ ክልል ያለውን የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ለማሻሻል እየተሰሩ የሚገኙ ሥራዎች ሊጠናከሩ ይገባል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሯ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሥራ ሃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅትም አሁን ያለውን የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ለማሻሻል በተለይ ተደራሽነቱን ለማሳደግ በትኩረት መስራት ይገባል ነው ያሉት፡፡

በክልሉ ሃይል የተቋረጠባቸው አካባቢዎች ሃይል እንዲያገኙ ለማድረግና አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል መስራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

የኤሌክትሪክ ሃይልን ተደራሽ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የክልሉ መንግስት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴዔታ ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) በበኩላቸው ÷ የኤሌክትሪክ ሃይልን በሚፈለገው ደረጃ ለማሕበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በብሄራዊ የኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም እየተሰራ ነው ብለዋል።

ከዋናው መስመር ርቀው ለሚገኙ አካባቢዎች የጸሃይ ሃይል ማመንጫዎችን በመጠቀም ሕብረተሰቡን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል።

የኤሌክትሪክ ሃይል ተደራሽነትን ለማጠናከር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስፈላጊውን ሥራ ለማከናወን ዝግጁ ነው ያሉት ደግሞ የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ አንዋር አብራር ናቸው፡፡

በኤፍሬም ምትኩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.