Fana: At a Speed of Life!

ከ15 ነጥብ 8 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን በላይ የገቢና ወጪ ጭነት ተጓጉዟል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በበጀት ዓመቱ 11 ወራት ከ15 ነጥብ 8 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን በላይ የገቢና ወጪ ጭነት ተጓጉዟል አለ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) የተቋሙን የ2017 በጀት ዓመት የ11 ወራት የዕቅድ አፈፃጸም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡

በሪፖርታቸውም ከ14 ነጥብ 2 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን በላይ ገቢ እቃዎች እንዲሁም ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን በላይ የወጪ ጭነት ተጓጉዟል ብለዋል፡፡

ከዚህም ውስጥ ከ2 ነጥብ 4 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ፥ በየዓመቱ እያደገ የመጣውን የማዳበሪያ አቅርቦት በወቅቱ ለማጓጓዝ ከፍተኛ ርብርብ ተደርጓልም ነው ያሉት፡፡

በተጨማሪም ከ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን በላይ ፈሳሽ ምርቶች መጓጓዛቸውን አንስተው÷ ይህም በበጀት ዓመቱ ከተያዘው እቅድ 96 በመቶ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

84 በመቶ የሚሆነው ጭነት በተሸከርካሪ፣ 14 በመቶ በባቡር እንዲሁም ቀሪው በአየር ትራንስፖርት መጓጓዙንም ነው ለምክር ቤቱ ያስረዱት፡፡

በሌላ በኩል የታለመለት የነዳጅ ድጎማን ሙሉ በሙሉ ማሳካት መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በሀገር አቀፍ ደረጃ 960 ሚሊየን ህዝብ ማጓጓዝ እንደታቸለ ጠቅሰው፥ የአንድ ሀገር አቋራጭ አውቶብስ አማካይ ሽፋን 105 ሺህ ኪ.ሜ ማድረሱን ተናግረዋል፡፡

በኃይለማርያም ተገኝ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.