Fana: At a Speed of Life!

አረንጓዴ አሻራ ብዝሃ ህይወት እንዲጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል – ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የደን ሽፋንን በማሳደግ ብዝሃ ህይወት እንዲጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል አሉ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)።

የኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት በዘርፉ የሚያከናውናቸውን ተግባራት በተመለከተ ከክልሎች ጋር ለመምከር ያዘጋጀው የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ኢትዮጵያ የብዝሃ ህይወት ሀብቶች እንዳሏት ከመግለጽ ባሻገር ዘርፉ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ የሚደረገውን ጥበቃ ማጠናከር ያስፈልጋል።

አብዛኛው የብዝሃ ህይወት የሚገኘው በደን ውስጥ በመሆኑ የደን ሽፋንን ማሳደግ እንደሚገባ ነው የገለጹት።

ኢትዮጵያ በየዓመቱ እያከናወነች ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የደን ሽፋንን በማሳደግ ብዝሃ ህይወት እንዲጠበቅ ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት በብዝሃ ህይወት ጥበቃ ላይ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን ተናግረዋል።

የብዝሃ ህይወት ጥበቃ ስራን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የክልል የግብርና ቢሮዎችና ተጠሪ ተቋማት ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በኃይለማርያም ተገኝ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.