በብሔራዊ ሙዚየም የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶች የኢትዮጵያን ገናና ታሪክ ያሳያሉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶች የኢትዮጵያን ገናና ታሪክ የሚያሳዩ ናቸው አሉ ሙዚየሙን የጎበኙ የጤና ሙያተኞች።
“ኢኖቬሽን ለሁለንተናዊ የጤና ሽፋን” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የጤና ኢኖቬሽንና ጥራት ጉባኤ የተሳተፉ ሙያተኞች ብሔራዊ ሙዚየምን ዛሬ ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም ሙዚየሙ የኢትዮጵያን ታሪክና ቅርስ በአንድ ላይ ሰንዶ እንደያዘ መመልከታቸውን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በሙዚየሙ የሚጎበኙ ቅርሶችና ታሪካዊ ጽሁፎች ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅ ጉልህ ፋይዳ እንዳላቸው ተገንዝቢያለሁ ያሉት ዶክተር ነጋሽ ስዩም፤ ታሪካዊ ቅርሶች ተደራጅተው መገኘታቸው የኢትዮጵያን ገናና ታሪክና ቀደምትነት ለማሳየት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ብለዋል።
ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አሚር አብደላ በበኩላቸው፤ ጉብኝቱ የኢትዮጵያን ታሪክና ቅርስ ለማወቅ እድል የሚፈጥር መሆኑን ጠቅሰው፤ ሙዚየሙን ማደስ ጨምሮ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች ኢትዮጵያ በፈጣን እድገት ላይ መሆኗን በተግባር የሚያሳዩ ስለመሆናቸውም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የባለ ብዙ ታሪክ፣ ባህልና የቱሪስት መዳረሻ መሆኗን ለሌሎች ለማሳወቅ በሙዚየሙ የተቀመጡ ታሪካዊ መዛግብትና ቅርሶች ጥሩ ማሳያ እንደሚሆኑ የገለጹት ደግሞ አቶ አበባው ደርሶ ናቸው።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!