የሀገር ሉአላዊነትን የሚያረጋግጠው አረንጓዴ አሻራ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የግብርና ሚኒስቴር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የምግብ ዋስትናን እና ሉአላዊነት በማረጋገጥ የሀገር ሉአላዊነትን ያረጋግጣል አለ።
በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃ እና አጠቃቀም መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ፋኖሴ መኮንን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለፁት፤ ለ7ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከበጋ ጀምሮ ዝግጅት ተደርጓል።
በዚህም 7 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ፣ የመትከያ ስፍራ ልየታ እና ጉድጓድ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።
ዘንድሮ ከሚተከሉት ችግኞች ውስጥ 40 ከመቶ የደን ሲሆን 60 ከመቶው ደግሞ ለምግብነት የሚሆኑ ፍራፍሬ፤ የእንስሳት መኖ እና ለአፈር ለምነት የሚያገለግሉ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
የአረንጓዴ አሻራ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለው ዲፕሎሚሲያዊ ግንኙነት እንዲጠናከር እና አረንጓዴ ኢኮኖሚ እንዲገነባ ማድረጉንም ገልፀዋል፡፡
የዘንድሮ የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚጀምር የጠቀሱት አቶ ፋኖሴ ሁሉም ህብረተሰብ የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጠይቀዋል።
“በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ የሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በትናንትናው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት መካሄዱ ይታወቃል።
በአልማዝ መኮንን
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!