የዕድሜ ምርመራ ካደረጉ 76 አትሌቶች መካከል 22 ብቻ አለፉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዕድሜ ምርመራ ካደረጉ 76 አትሌቶች መካከል በድምሩ በሁለቱም ፆታ 22 አትሌቶች ብቻ ምርመራውን አልፈዋል አለ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፡፡
በናይጄሪያ በሚካሄደው የወጣቶች ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉ አትሌቶች የዕድሜ ምርመራ ኤምአር አይ (MRI) ውጤት ይፋ ሆኗል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በፈረንጆቹ 2025 ከሐምሌ 16 እስከ 20 ድረስ በናይጄሪያ አቡኩታ ከ18 ዓመት በታች እና ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፉ አትሌቶች ዕድሜ ምርመራ አከናውኗል።
ፌዴሬሽኑ በአጠቃላይ በሁለቱም ፆታ ለ76 አትሌቶች የዕድሜ ምርመራ አድርጓል።
በዚህም መሰረት የዕድሜ ምርመራውን ካደረጉ 76 አትሌቶች መካከል በሁለቱም ፆታ በድምሩ 22 አትሌቶች ምርመራውን አልፈዋል።
ምርመራውን ያለፉት 6 ወንድና 16 ሴት አትሌቶች መሆናቸውን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!