Fana: At a Speed of Life!

በጤናው ዘርፍ ሕይወት አድን ቴክኖሎጂዎችን ይበልጥ ለማቅረብ እየተሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በጤናው ዘርፍ ሕይወት አድን ቴክኖሎጂዎችን ለማኅበረሰቡ ይበልጥ ለማቅረብ እየተሰራ ነው አሉ፡፡

የካንሰር ህክምና ተደራሽነትን ማሳደግ ላይ ያተኮረው ‘ሬይስ ኦፍ ሆፕ 2025’ ዓለም አቀፍ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፎረሙ መክፈቻ ላይ እንደገለጹት÷ ባለፉት 30 ዓመታት በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ኢትዮጵያ ታሪካዊ ሥራን አከናውናለች።

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የማኅበረሰብ ጤና ባለሙያዎችን አሰልጥነናል በማለት ገልጸው÷ ጤናን የልዩ ጥቅም ጉዳይ ሳይሆን መብት በማድረግ የአገልግሎት ተደራሽነትን ወደ ሁሉም የሀገሪቱ ማዕዘናት አስፋፍተናል ብለዋል።

የካንሰር ሕክምና ማዕከል ተደራሽነት እየሰፋ እንደሆነና የራዲዮቴራፒ አገልግሎት ተደራሽነትን በክልሎች ለማስፋት እየተሰራ መሆኑን አንስተው÷ የጨረራ ሕክምና ሥራ ይበልጥ በኃላፊነት እና ደሕንነቱ በተጠበቀ መልኩ እንዲሰራ የሕግና የቁጥጥር ሥራዎች መጠናከራቸውን ተናግረዋል።

የአረንጓዴ አሻራ የመሬት ሀብትን እያከመ የኅብረተሰብ ጤና ሁኔታን እያሻሻለ መሆኑን ገልጸው÷ በተለዩ ቀናት፣ በተለዩ መንገዶች እና አካባቢዎች የሚደረጉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ልምዶችን እያስተካከሉ እና ጤናማ አኗኗርን እያለማመዱ ነው ሲሉም አብራርተዋል።

ከሁሉም ፖሊሲዎች ጀርባ ሰው እንዳለ እናስብ፤ ከሁሉም ኢንቨስትመንቶች ጀርባ ሕይወት አለ፤ ከሁሉም መዘግየቶች የእናቶች ጥበቃ አለ ያሉት አቶ ተመስገን ጥሩነህ÷ ሊታከም በሚችል ካንሰር የትኛውም ሕይወት ማለፍ የለበትም ሲሉም አጽንዖት ሰጥተዋል።

ታማሚ በአካባቢ ርቀት ወይም በገንዘብ ችግር ከነሕመሙ በቤቱ ቀርቶ መሰቃየት እንደለሌበት አንስተዋል።

ፎረሙ ከሦስት ዓመታት በፊት ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ የካንሰር ሕክምናን ለማሳደግ ”ሬይስ ኦፍ ሆፕ” የተስፋ ወጋገን በሚል መርህ የካንሰር ህክምናን ለማዳረስ ባስጀመረው ተግባር አፈጻጸም ላይ የሚመክር እንደሆነ ተገልጿል።

በለይኩን ዓለም

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.