Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ዞን በ5 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የተገነቡ 1 ሺህ 886 ፕሮጀክቶች ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን በ5 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነቡ 1 ሺህ 886 ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀዋል፡፡

የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ትጃኒ ናስር ÷ በጅማ ዞን ደዶ እና ቀርሳ ወረዳዎች የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

በዚህ መሰረትም በዴዶ ወረዳ ከ40 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በ176 ሚሊየን ብር ተገንብቶ ለአገልግሎት መብቃቱን አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም በቀርሳ ወረዳ ከ50 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ፣ የእንስሳት እርባታ ማዕከል እና የሌሎች ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጠናቅቆ መመረቁን ጠቅሰዋል፡፡

ፕሮጀክቶቹ ከ200 ሺህ በላይ የማሕበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሲሆን÷ከ16 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ እድል እንደፈጠሩም አብራርተዋል፡፡

በአጠቃላይ በዞኑ በ5 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነቡ 1 ሺህ 886 ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውን ነው የገለጹት፡፡

በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነመራ ቡሊ በበኩላቸው ÷ በበጀት ዓመቱ በክልሉ 2 ሺህ 960 የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች በ14 ቢሊየን ብር ተገንብተው ለአገልግሎት መብቃታቸውን ተናግረዋል።

በተስፋሁን ከበደ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary

በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.