Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ማስጀመሪያ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች እና ከተሞች የ2017 ዓ.ም አረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ‘በመትከል ማንሰራራት’ በሚል መሪ ሃሳብ ተጀምሯል፡፡

ክልሉ በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሚሰጡ ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት አድርጓል።

በ38 ሺህ የችግኝ ጣቢያዎች የተዘጋጁና ለደን ልማት፣ ለእንስሳት መኖ፣ ለአፈር ለምነት መጠበቅ እንዲሁም ለምግብነት የሚውሉ ችግኞች በ1 ነጥብ 1 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ ይተከላሉ።

ባለፉት ስድስት ዓመታት ከ6 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት ላይ የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች በክልሉ የተተከለ ሲሆን፤ ከተተከሉ ችግኞች መካከል 88 በመቶ የሚሆኑት ጸድቀዋል።

የአረንጓዴ ልማት ሥራው የውሃ አማራጮች እንዲሰፉ፣ በተፈጥሮ ሀብት መራቆት የደረቁ ሐይቆችና ወንዞች መልሰው እንዲያገግሙ አድርጓል።

በተጨማሪም የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ የአርሶ አደሩን ምርታማነት በማሳደግ የምግብ ዋስትና እንዲረጋገጥ ማድረጉንም የክልሉ ግብርና ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.