ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ነገ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነገ ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስትን የ2017 የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ የሚሰጡ ይሆናል፡፡
በተጨማሪም የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምክር ቤቱ ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡