Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሠራዊት አባላትን የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመከላከያ ሠራዊት አባላትን የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን የሠራዊት የጋራ መኖሪያ ቤት ጎብኝተዋል፡፡

የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታውን በፍጥነትና በጥራት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ብርጋዲየር ጀኔራል ደረጀ መገርሳ ተናግረዋል፡፡

ለዚህም ዘመኑን የዋጁ የግንባታ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በትብብር እና በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን ነው ያስረዱት፡፡

የሠራዊቱን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ማሟላት የአባላቱን የግዳጅና ተልዕኮ አፈጻጸም ብቃት ለማሳደግ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የመከላከያ ሠራዊት አባላትን የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስገንዝበዋል፡፡

የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ግንባታ ሲጠናቀቅ መስፈርቱን ለሚያሟሉ የሠራዊት አባላትና ሲቪል ሠራተኞች በእጣ እንደሚተላለፉም የመከላከያ ሠራዊት ኦንላይን ሚዲያ ዋና አዘጋጅ ሌ/ኮ ውብሸት ቸኮል ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.