Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የጋዝ ምርት ለመጀመሪያ ጊዜ የፊታችን መስከረም ወር ላይ ለገበያ ታቀርባለች – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የጋዝ ምርት የፊታችን መስከረም ወር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ለገበያ ታቀርባለች አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤቱ 42ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው የመንግስትን የ2017 የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡

በማብራሪያቸውም በለውጡ መንግስት ጋዝ ለማምረት ፋብሪካዎች ለመትከል ስምምነት ተደርጎ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ጋዝና አካባቢ የሚመጡ የግል ድርጅቶች እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የነበራቸው ፍላጎት ፈቃድ መውሰድና በዛ ፈቃድ ብር መፈለግ ነበር ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ ይህ አካሄድና መንገድ አያዋጣም ብለን የነበሩትን በመሰረዝ አዳዲስ ኩባንያዎች ወደ ዘርፉ እንዲገቡ አድርገናል ነው ያሉት፡፡

ይህን ተከትሎም ምናልባትም የምክር ቤት አባላት ከእረፍት ሲመለሱ የፊታችን መስከረም ወር ላይ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የጋዝ ምርት ለገበያ ታቀርባለች ብለዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.