Fana: At a Speed of Life!

ቤተክርስቲያኗ ከምክክር ኮሚሽን ጎን በመሆን ድጋፏን አጠናክራ ትቀጥላለች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጎን በመሆን ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋገጠች።

የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዛሬው ዕለት የምክክር አጀንዳዎቿን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረክባለች።

የቤተክርስቲያኗን አጀንዳዎች የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ ከሌሎች ብጹዓን አባቶች ጋር በመሆን ነው ያስረከቡት።

ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) በዚሁ ወቅት÷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምክክር ሂደቱ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን አንስተዋል።

ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ በበኩላቸው÷ በምክክሩ ሂደት ላይ ቤተክርስቲያኗ የነበራት ቅሬታ ተቀርፎ በአግባቡ እየተሳተፍን ነው ብለዋል።

ኮሚሽኑ ሀገርን የሚያሻግር ሥራ እያከናወነ መሆኑን ገልጸው÷ በሁሉም የምክክር ሂደት እርከኖች እንድንሳተፍ እንዲሁም አጀንዳዎቻችንን በዚህ መልኩ አደራጅተን እንድናቀርብ እድል ስለሰጠን በቤተክርስቲያኗ ስም እናመሰግናለን ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የቤተክርስቲያኗ አጀንዳዎች ለሀገርና ለሕዝብ ሰላም መረጋገጥ ጉልህ ሚና እናዳላቸው የገለጹት ብፁዕ አቡነ ፍሊጶስ የተጀመረውን ሰላም የማረጋገጥ ጉዞ እንዲሳካ ከኮሚሽኑ ጎን በመሆን ድጋፏን አጠናክራ ትቀጥላለች ማለታቸውን አቶ ጥበቡ ተናግረዋል።

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.