Fana: At a Speed of Life!

ፍርድ ቤቱ የአቶ ጃዋር መሃመድን የዋስትና ጥያቄን ውድቅ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋር መሐመድ ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አደረገ።

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በልደታ አዳራሽ የአቶ ጃዋር መሃመድን ጉዳይ ተመልክቷል።

አቶ ጃዋር መሃመድ ከዚህ ቀደም በተሰጠው የጊዜ ቀጠሮ መረሰት ነው በዛሬው እለት ከአንድ ጠበቃ ጋር ፍርድ ቤት የቀረቡት።

መርማሪ ፖሊስ በአቶ ጃዋር መሃመድ ላይ የሚያደርገውን ምርመራ መዝገብ ማጠናቀቁን ገልጾ፤ አቃቤ ህግ በከፈተው ቅድመ መርመራ መዝገብ እንዲቀርቡልኝ ሲል በጽሁፍ አቤቱታ አቅርቧል።

የአቶ ጃዋር መሃመድ ጠበቃ በበኩላቸው “መርማሪ ፖሊስ ምርመራዬን አጠናቅቄያለሁ ብሏል፤ የተጠርጣሪውን ዋስትና የሚያስከለክል ደረጃ ማስረጃ ስላላቀረበ ዋስትና ይፈቀድላቸው” ሲል ጠይቋል።

ጉዳዩን የተመለከተው ፍርድ ቤቱም ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ክስ ቢቀርብ የሰው ህይወት ባለፈበት ወንጀል የተጠረጠሩ  መሆኑን ተከትሎ እስከ 15 ዓመት የሚያስቀጣ መሆኑን ካለው ድንጋጌ መረዳት ይቻላል ብሏል።

በዚህም ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ ያደረገ ሲሆን፥ መዝገቡም ወደ መዝገብ ቤት እንዲመለስ አዟል።

በታሪክ አዱኛ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.