ኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል ቁርጠኛ ናት – ፕሬዚዳንት ታዬ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚደረጉ ትብብሮችን ለማጠናከር ቁርጠኛ ናት አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፡፡
ፕሬዚዳንት ታዬ ከዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት (ኢንተርፖል) ፕሬዚዳንት አሕመድ ናስር አል ራይዚ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ታዬ በዚህ ወቅት እንዳሉት ፥ ኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚደረጉ ትብብሮችን ለማጠናከር ቁርጠኛ ናት፡፡
ኢንተርፖል የሀገራትን የፖሊስ ተቋማት በማስተባበር ረገድ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ ማድነቃቸውንም የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡